የልማት ደርጅቱ ሀላፊ ተሰማ በቀለ (ዶ/ር) እንደገለፁት በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት መደበኛ ትምህርት በመቋረጡ ቀደም ሲል ድጋፍ ይደረግላቸው የነበሩ ተማሪዎች እና ወላጅ እናቶቻቸው በኮቪድ19 ምክንያት ለኢኮኖሚያዊ ችግር በመጋለጣቸው እነሱን ለመደግፍና አለኝታነትን ለማሳየት የልማት ድርጅቱ የሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺ (375,000) ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል ፡፡ ሀላፊው አክለውም ደርጅቱ ወላጅ አልባ ህፃናትን በማሳደግ፣ለት/ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት፣ የተማሪዎች መጸዳጃ ቤት በመገንባት፣ከሶስት ሺ በላይ የኑሮ ጫና ያለባቸው ሴቶችን በማገዝና ሌሎች በርካታ የማህበረሰብ በጎ ተግባራትን እያከናወነ ያለ የልማት ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አማኑኤል የልማት ደርጅት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለኢኮኖሚያዊ ችግር ለተጋለጡ አምስት መቶ ወላጅ እናቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የልማት ደርጅቱ ሀላፊ ተሰማ በቀለ (ዶ/ር) እንደገለፁት በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት መደበኛ ትምህርት በመቋረጡ ቀደም ሲል ድጋፍ ይደረግላቸው የነበሩ ተማሪዎች እና ወላጅ እናቶቻቸው በኮቪድ19 ምክንያት ለኢኮኖሚያዊ ችግር በመጋለጣቸው እነሱን ለመደግፍና አለኝታነትን ለማሳየት የልማት ድርጅቱ የሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺ (375,000) ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል ፡፡ ሀላፊው አክለውም ደርጅቱ ወላጅ አልባ ህፃናትን በማሳደግ፣ለት/ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት፣ የተማሪዎች መጸዳጃ ቤት በመገንባት፣ከሶስት ሺ በላይ የኑሮ ጫና ያለባቸው ሴቶችን በማገዝና ሌሎች በርካታ የማህበረሰብ በጎ ተግባራትን እያከናወነ ያለ የልማት ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት አማኑኤል የልማት ድርጅት በክፍለ ከተማው ያለውን አኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግርን ለመደገፍ በክፍለ ከተማው የተወሰኑ ወረዳዎች ላይ እያደረገ ካለው ድጋፍ ጎን ለጎን አሁን እንደ ሀገር ያጋጠመውን ችግር ለመጋራትና ለተቸገሩ ወላጅ እናቶች አለኝታውን በማሳየቱ በክፍለ ከተማው ስም አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኮረና ወረርሽኝ መደበኛውን የመማር ማስተማር ስራ ከማስተጓጎል ጀምሮ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ችግሮች የፈጠረ ቢሆንም፤ የገጠመንን ችግር በጋራ ሆነን ለማለፍ ለሚደረገው የእርስ በርስ መደጋገፍ የበጎ አድራጎት አካላት ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

More Pictures on COVID-19 Donation